Dr. Fekadu Bekele has a Master’s degree in National Economics and has earned his Doctorate in Development Economics. He is from Ethiopia and has studied in Germany at the Free University of Berlin, University of Siegen, and at the University of Essen. As a part-time lecturer, he taught at the Free University of Berlin, at the Technical and Economics University of Berlin, and at the University for Economics in Berlin(an der Fachhochschule für Wirtschaft in Berlin). He has taught International Trade Theory, Development Economics, International Debt, International Currency systems, and about the role of the International Monetary Fund and the World Bank, in the Third World countries, especially in Africa. He has also given lectures and seminars at various institutions in Berlin. He has published several articles about development economics, international politics, and the economic and social challenges of many African countries. He has also published different books, namely, “African Predicaments and the Method of solving them effectively” as well as a “German-Amharic dictionary” in collaboration with his wife, and a book about the “Genesis and Development of Capitalism and the foundation of Political Economy” in Amharic language.
Though many articles that are posted on this website are written in the Amharic language, I try to raise a variety of issues that are also relevant, especially to many African countries. The fact that I came to Germany and got a chance to study national economics and development economics, gave me a unique opportunity to make myself acquainted with the intellectual history of Europe, especially that of Germany. I began then questioning the relevance of my qualification in bringing Ethiopia and other African countries out of poverty and underdevelopment. I have tried to reexamine my studies at the university and compared it with a variety of economic literature that was developed and written by highly intellectually minded German scholars that thought differently from the mainstream. The Germany scholars of the 18th and 19th centuries thought holistically and stressed the relevance of rational thinking as a tool to grasp any society not only as an arena of economic activity but also many diverse activities that are the products of the human mind. In other words, human beings must not be reduced to mere producers and consumers, but should also be seen as cultural, ethical, and social beings. Unfortunately, this kind of thinking that the German philosophers and poets have developed and preached is not integrated into economic textbooks. Not only in Germany but also across the globe the neoclassical and Neoliberal schools of thought that have their origin in England and Austria became the lingua franca of those experts that formulate economic policies for African and other Third World countries. Economic thoughts that were developed by Mercantilists, by critical social thinkers like Sismondi de Sismondi, by national economists like Friedrich List who vehemently criticized the classical doctrine of Adam Smith and Ricardo, especially their doctrine about the international division of labor, and by radical thinkers like Karl Marx who systematically analyzed about the genesis of capitalism, its development from simple commodity production to an expanded form of production, and its contradictory movements, etc. are excluded from the university curriculum. Students like me who come from a different social formation and very backward countries, as long as they do not pose questions about the relevance of this kind of one-sided economic thinking in solving the complex problems of their countries, they rather strengthen the existing social realities. Instead of eradicating poverty and hunger, they rather deepen them. It is not without reason that after 60 years of political independence why we see chaotic situations in many African countries.
Through the philosophical and science-related books that are written form different perspectives, I realized then that the neoclassical economic doctrine that I was brought up has no relevance in bringing a genuine development in Ethiopia and other African countries. Instead of bringing light to the mind, it darkens the mind. Neoclassical and Neoliberal theories cannot, therefore, enable somebody to read social realities that exist on the ground and political relationships that prevail in any given country correctly. The debate about development and underdevelopment and the controversial discussions about the transformation of capitalism from feudalism that were raised and debated by Marxist scholars and other enlightened intellectuals prove my judgment. I realized then how global capitalism and its actors put everything on their heads and make things very complicated to innocent people in many Third World countries. The political, economic, and military elite in many African countries, and also in my country is simply the victim of such kind of badly formulated education system. Why dictatorship and bad governance are the dominating factors in many African countries should not be then a secret to many who read all my articles. Dictatorship and bad governance are by-products of global capitalism. Therefore, the chaotic political, economic, and social situations in many African countries are merely the products of global capitalism. Global capitalism extracts wealth and transfers it to the western metropolis when the situations in many African countries are chaotically organized. The wars in many different parts of Africa, the war that is being waged under the pretext of fighting Islamic terrorism is nothing else other than diverting the attention of African governments from real economic and social developments. Therefore, global capitalism undermines true human freedom, solidarity, and peace.
From this vantage point, I tried to develop my view of how a genuine economic development should look like. A genuine development should and must incorporate philosophy, politics, economics, sociology, arts, architecture, and in general what we call culture. In short, development should not be seen detached from spiritual and intellectual activities. Economic development that is detached from this kind of thinking will lead sooner or later to catastrophe. All articles that are posted on this website are written from this point of view and are educational by nature. Those who visit and read the articles find very important concepts like rational thinking and awareness, that are very relevant to all human lives. In short, the messages of the articles are purely educational and can be tested through philosophical and true economic books.
In my book African predicaments and the method of solving them effectively, I tried to show how a genuine economic development should look like. Most of the articles that are posted on this website entail more or else the same strategic concepts.
- All African countries need political reforms. Without political reforms and without mass participation in the political process there cannot be genuine economic development.
- The masses in each African country must be organized at various levels to solve their problems. Workers, peasants, youth, and women should be organized to address their problems.
- African governments should introduce a literacy campaign. When people can read and write they can articulate better and could challenge local authorities.
- To make the literacy campaign more effective, it must be supported by special kinds of public schools, that comprehend a variety of specializations that enable the participants to solve their problems. The democratization of the political process can only be possible when the masses are being equipped with the necessary knowledge.
- To mobilize human and natural resources, African countries need effective and modern institutions. Institutions have also binding and stabilizing aspects. Community building and other grass-root organizations can only be possible when there are public institutions at local, and regional levels.
- The entire political process should be supported by an education system that enables students to raise questions and solve problems.
- To bring a genuine social and economic development in each African country African governments should abandon the Neoliberal economic policy. With a Neoliberal economic policy, one cannot create true national wealth and eradicate poverty.
- An inward-looking strategy is the most effective policy that can eradicate poverty and reduce unemployment.
- The main aim of a genuine economic policy should be to solve the basic-needs problems of a given society. Self-sufficiency in food, clean water, proper housing, and introducing a health care system that also incorporates traditional or alternative medicine are the issues that any government should give priority.
- To solve the cultural, economic, and social crises that prevail in each African country, African governments should rely on themselves and their people.
- Foreign aid and advice cannot solve African problems. They rather worsen the situation.
- The main aim of the entire policy should be to create a new society, that is based on solidarity, mutual respect, social responsibility, ecological awareness, and political consciousness.
ሰላምና ዕድገት ለሚስፍንባት!
ዲሞክራሲ ለሚያብባት!
የሰው ልጅ መብት ለሚከበርባት!
እያንዳንዱ ግለሰብ ማንነቱን ለሚያውቅባት!
አንዱ ለሌላው አለኝታ ለሚሆንባት!
እጅ ለእጅ ተያይዞ አዲስ ኢትዮጵያን ለመገንባት!
ይህ ነው የዚህ ድረ-ገጽ ዋናው መልዕክት!
መግቢያ
በአገራችን ምድር ለዲሞክራሲና ለነፃነት፣ እንዲሁም ለዕድገት እየተባለ ከአርባ ዐመታት በላይ የሚቆጠር ብዙ መስዋዕትነትን የጠየቀ ትግል ተካሂዷል። በዕድሜያችን ከሶስት በላይ አገዛዞችን አይተናል። አሁን አራተኛው ላይ እንገኛለን። ከፊዩዳሉ ስርዓት ለመላቀቅና ዕውነተኛ የሆነ በሳይንስና በቴክኖሎጂ ላይ የተመሰረተን ዕድገት ማየት አስፈላጊና የጊዜው አንገብጋቢ ጥያቄ ቢሆንም ምሁሩና ህዝባችን የተመኙት ነገር በተግባር አልተመነዘረም። የሞናርኪው አገዛዝ ከወደቀና የፊዩዳሉ ስርዓት ከተገረሰሰ በኋላ ህዝባችን አንድም ጊዜ እፎይ ብሎ ያረፈበትና በሰላም ለመንቀሳቀስ ዕድል ያገኘበት ጊዜ የለም። በነፃነትና በዲሞክራሲ ፈንታ እርስ በእርስ መገዳደል፣ የአገር እሴት መበጣጠስና የብሄራዊ ውርደት በመተካት የአገራችን አንድነት አስጊ በሆነ ሁኔታ ውስጥ እንዲወድቅ ተደርጓል። ከንጉሳዊው አገዛዝና ከፊዩዳሉ ስርዓት ይልቅ ምሁር ነኝ ባዩና በተለያየ ጊዜ ስልጣንን የተቆናጠጡት፣ ከደርግ አገዛዝ ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ ያሉት አገዛዞች ኢሰብአዊና አገርን በታታኝ እንዲሁም አስበዝባዥ እየሆኑ ነው የመጡት። እስካሁን ድረስ የነፃነትን አርማ ይዘው የታገሉና ስልጣንን የተቀዳጁትም ሆነ ስልጣንን የመቀዳጀት ዕድል ያላገጠማቸው አሁንም ቢሆን በህይወት የሚገኙም ለምን አረመኔ እየሆኑና አገር በታኝ እየሆኑ ለመምጣት እንደቻሉ እስካሁን ድረስ ይህንን በሚመለከት ምርምር አልተደረገም። ከብዙዎች የሚሰማዉ ይህ ሁሉ ነገር ሊደርስ የቻለው አንድም ምሁሩ የውጭ ርዕዮተ-ዓለም በመከተሉ ነው የሚል ሲሆን፣ በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ ምሁሩ መግባባት ስላልቻለ ነው የሚል ነው። ይህንን ዐይነቱን „አሳሳች ርዕዮተ-ዓለም“ ለምን ምሁሩ ተከተለ? ማንስ አስገደደው? ለምንስ አይግባባም? የሚሉትን ጥያቄዎች እያነሳ ለመመራመር የሞከረ የለም።
ይህንን አስቸጋሪ ጉዳይ ለመረዳት የዚህ ድህረ-ገጽ አዘጋጅና ባለቤት ከ20 ዐመታት በላይ የፈጀ ምርምር አድርጓል። ከእሱ ከሚበልጡ የውጭ አገር ምሁራንም ጋር ተወያይቷል፤ በቂ ትምህርትም ቀስሟል። በእኔም ሆነ በብዙዎች ዘንድ የተደረሰበት መልስ በእኛ አገርም ሆነ በአብዛኛዎቹ የአፍሪካና የላቲን አሜሪካ አገሮች ውስጥ ጭንቅላትን የሚያድስና ልብን ርህራሄ የሚያደርግ ሰፋና ጠለቅ ያለ ምሁራዊ እንቅስቃሴና ክርክር ለመካሄድ ባለመቻሉ ለነፃነት እንታገላለን ብለው የሚነሱና በአጋጣሚም ስልጣንን የሚጨብጡ ኃይሎች የራሳቸው አጭርና በጣም ጠባብ የሆነ አስተሳሰብ ሰላባ በመሆን ከነፃነትና ከዲሞክራሲ ይልቅ ጭቆናንና ብዝበዛን ያሰፍናሉ የሚል ነው። የጨበጡትን የመንግስት መኪና ተገንና መሳሪያ በማድረግና ማንአለብኝ በማለት አንድን ህዝብ መቆሚያና መቀመጫ ያሳጡታል፤ የአገር ሀብትም እንዲበዘበዝና እንዲባክን ያደርጋሉ። በዚህም ምክንያት የተነሳ የሰፊው ህዝብ መሰረታዊ ፍላጎቶች፣ ንጹህ ውሃ፣ መጠለያ፣ በቂና የተሟላ ዲዬት፣ ትምህርትና ህክምና የመሳሰሉት ለሰው ልጅ መኖር በጣም አስፈላጊ የሆኑ ነገሮች ከመሟላት ይልቅ ሰፊው ህዝብ በአዲስና የታሪክና የባህል ግንዛቤ በሌላቸው የፖለቲካ፣ የሚሊታሪና የኢኮኖሚ ኤሊቶች ይገፈተራል፤ ይበዘበዛልም። ኤሊቱ ከውጭ ኃይሎች ጋር በመቆላለፍና ታዛዥ በመሆን በገዛ ህዝቡ ላይ ጦርነት ያውጃል። የራሱን ህዝብ ከሰው በታች እንዲኖር ያደርገዋል። ስለሆነም ስቴዬፓን ሜስትሮቪክ የሚባለው የሶስይሎጂና የፈላስፋ ምሁር እንደሚለው በየአገሮች ውስጥ አረመኔያዊ ባህርይ(Barbarian Temprament) ያላቸው ሰዎች ስልጣንን በመቆናጠጥ ወይም ደግሞ ስልጣንን ከጨበጡ በኋላ ወደ አረመኔነት በመለወጥ በተለይም የነቃውን የህብረተሰብ ክፍል ያስራሉ፤ ያሰቃዩታል፤ ወይንም ደግሞ የሆነ ያልሆነ ምክንያት በመፈለግ አገሩን ጥሎ እንዲወጣ ያደርጋሉ። ህዝቡም እፎይ በማለትና የመንፈስ ነፃነት በመቀዳጀት የራሱን ህይወት እንዳይመራና የሳይንስና የቴክኖሎጂ ባለቤት እንዳይሆን ያደርጉታል። ህይወቱ በሙሉ ከጦርነት ጋር እንዲያያዝ በማድረግ በዘለዓለማዊ ፍርሃት እንዲዋጥ ያደርጋሉ። ይህ ዐይነቱ እጅግ አስቀያሚና አስከፊ ሁኔታ የተፈጠረውና የሚፈጠረው ዕውቀት ተስፋፍቷል፤ የሰው ልጅም በሳይንስና በቴክኖሎጂ አማካይነት ህይወቱን ለማቃለል ይችላል በሚባልበት ዘመንና ሳይንስና ቴክኖሎጂ ባበቡበት ዘመን ነው። በካንትም ሆነ በሄገል ዕምነት የሰው ልጅ ከተማዎችን በገነባና ሳይንስንና ቴክኖሎጂን እየተቀዳጀ በመጣ ቁጥር የበለጠ ስለሚገለጽለት የሊበራል-ዲሞክራሲን ስርዓት የመመስረትና የሲቪል ህብረተሰብን የመቀዳጀት ዕድሉ ከፍ ይላል ይላሉ። ካንትም ሆነ ሄገል የሰውን ልጅ ሁኔታ ለመደንገግ የሚችለው አዕምሮው ነው ከሚለው በመነሳትና በታሪክ ሂደት ውስጥም ንቃተ-ህሊናው የሚዳብርና ሰው መሆኑን እየተገነዘበ ስለሚመጣ ድርጊቱ ሁሉ በአርቆ-አሳቢነት ላይ የተመሰረተ ነው ይሉናል። አንድን ነገር ከማድረጉ በፊት ማመዛዘን ይችላል ይላሉ። ይሁንና ሾፐንሃወር የሚባለው ፈላስፋ በዚህ ዐይነቱ የካንትና የሄገል አባባል አይስማማም። ጭንቅላት ብቻውን አንድን ሰው ወይም ህዝብ አርቆ-አሳቢና ርህሩህ አያደርገውም ይላል። ስለዚህም የልብን ማዕከላዊ ቦታ በማስመር የሰው ልጅ የሚራራና የሚፀፀት መሆን እንዳለበት በማሳሰብ ከሚያየው አሻግሮ በመሄድ ማሰብና ሚናውን መረዳት እንዳለበት ያስገነዝባል። ያም ሆኖ ይላል ሾፐንሃወር የሰው ልጅ ሙሉ በሙሉ ከአረመኔያዊው ባህርዩ ሊላቀቅ በፍጹም አይችልም። አረመኔያዊነትና ስልጣኔ እዚያው በዚያው ያሉ ነገሮች ስልሆኑ የሰው ልጅ ህይወት በሁለቱ መሀከል የሚዋልል እንደሆነ ያረጋግጣል። በፈለገው ዐይነት የሶሻል ኢንጂነሪግ ወይም ስርዓት አንድን ማህበረሰብ ሙሉ በሙሉ ከወንጀል ነፃና መንግስታትም ፍጹም ሊበራል ሊሆኑ አይችሉም በማለት የእነካንትንና ሄገልን አባባል ያጣጥላል። ሲግሙንድ ፍሮይድ የሚባለው የሳይኮሎጂ ተመራማሪም በሾፐንሃወር አባባል ሙሉ በሙሉ ይስማማል። እንዲሁም አዶርኖና ሆሮክሃይመርም ኔጋቲቭ ወይም ፀረ-ዲያሌክትክ በሚለው ምርምራቸው ላይ የሾፐንሃወርን አስተሳሰብ በመጋራት እንደምሳሌነት የጀርመንን የናዚ አገዛዝን አነሳስና የስድስት ሚሊዮንን የይሁዶች ህይወት ማለቅ በመጥቀስ የካንትንና፣ በተለይም የሂገልን አስተሳሰብ ይቃወማሉ።
ወደ አገራችን ስንመጣ ባለፉት አርባ ዐመታት በአገራችን ምድር የተከሰተው አሰቃቂ ሁኔታና ዛሬ ደግሞ አገራችን ያለችበት አደገኛ ሁኔታ ዋናው ምክንያት ጭንቅላቱ በደንብ ያልዳበረና ልቡ በርህራሄ ያልታነፀ ስልጣንን በመቀዳጀቱ ነው። የታሪክን ውጣ ውረድነት ሳያገናዝብ ስልጣንን የተቀዳጀ ኤሊት ታሪክን ከመስራትና ህዝቡን የሳይንስና የቴክኖሎጂ ባለቤት ከማድረግ ይልቅ በማንአለኝበት እራሱ ያወጣውን ህገ-መንግስት በመጣስ አገርን ያከረባብታል፤ በድብቅም ሆነ በይፋ የሰው ህይወት እንዲጠፋ ያደርጋል። ከዚህ በተጨማሪ ይህ ዐይነቱ የሚመስል በየኤፖኩ ስልጣንን የሚጨብጥ ኃይል በእራሱና በህዝብ ላይ ስለማይተማመን በዓለም አቀፍ ደረጃ በተዘረጋው የጭቆና አገዛዝ ሰንሰለት ውስጥ በመካተትና ታዛዥ በመሆን በህዝብ ላይ ግፍን ያደርሳል። በሌላ ወገን ግን ዕውቀት የሚባለውና እንደመመሪያ የሚወሰደው ፖሊሲ ሁሉ ከውጭ የሚመጣ ስለሆነ ምሁሩም ሆነ ስልጣንን በአንዳች ሁኔታ የሚቀዳጅ የዕውቀትን አመጣጥና የርዕዮተ-ዓለም መሰረት፣ እንዲሁም ከየትኛው ህብረተሰብ አንፃር እንዳደበረ ስለማያውቁ በአወቅኹኝ ባይነት በህዝብ ላይ ይጭናሉ። እንደዚህ ዐይነቱ ሳይጣራና ሳይመረመር ከውጭ የገባ ዕውቀትም ሆነ ፖሊሲ ህዝብን ከድህነት ከማውጣትና አገርንም ከማበልፀግ ይልቅ የባሰውን የሚያደኸይ ይሆናል። በአገራችንም ሆነ በብዙ አፍሪካ አገሮች የሚታየው አሳዛኝ ሁኔታ ከዚህ ዐይነቱ ዕውቀትንና ፖሊሲን በደንብ ሳይመረምሩ ከውጭ ከሚገባው ጋር በጥብቅ የሚያያዝ ነው። ስለሆነም ባለፉት 28 ዐመታት ይህንን ዐይነቱን የግፍ አገዛዝ ህዝባችን እንዲጋፈጥና እንዲሰቃይ የተደረገው በአብዛኛው ጎኑ ከንቃተ-ህሊና ማነስ ወይንም አለመዳበር የተነሳ ነው። በደንብ ያልነቃና ያልዳበረ ጭንቅላት ደግሞ መጠየቅ ስለማይችል ስልጣንን በመጨበጡ ብቻ ምስኪኑን ህዝብ በግፍ ይገድላል ወይም ያስራል። ካሊያም ደግሞ አገሩን ጥሎ እንዲሰደድ ያደርጋል።
ይህ ዐይነቱ የግፍ አገዛዝ በእኛ አገር ብቻ ሳይሆን በብዙ የሶስተኛው ዓለም አገሮች አፍጦ አግጦ ያለ ሀቅ ነው። ጭቆናውና ግፉም ሆነ ክትትሉ በተዘዋዋሪ ሰልጥነናል በሚባሉ የምዕራብ አውሮፓ የካፒታሊስት አገሮችም ውስጥ እየተዛመተና የፖለቲካ ሆኔታውን በአዲስ መልክ እንዲጻፍ እያደረገ ነው። በካፒታሊስት አገሮች ቀኝ ወይም ፖፑሊስት ፓርቲዎች እንደ አሸን በመፍለቅና በመጠናከር ፖለቲካው ወደ አደገኛ አቅጣጫ እንዲሄድ ለማድረግ እየጣሩ ነው። ባለፉት ሰባ ዐመታት የተለያየ ስም ይዘው የካፒታሊስት አገሮችን ይገዙ የነበሩ ፓርቲዎች ሚናቸው እያለቀና በካፒታሊዝም ውስጣዊ-ኃይል የተነሳ እየተዳከሙና እየተበታተኑ በመምጣት ላይ ናቸው። በተለይም በገንዘብ ክምችት የናጠጡ ትላልቅ የሃይ-ቴክ ኩባንያዎችና ሌሎች ኢንዱስትሪዎች አብጠው በመውጣት ባለፉት 50ና 60 ዐመታት እንደተለመደው መንግስታትም ሆነ ስልጣንን የሚጨብጡ ፓርቲዎች በቀላሉ የጣልቃ-ገብ(Interventionist)የኢኮኖሚ ፖሊሲ ተግባራዊ ሊያደርጉ የሚችሉበት ሁኔታ እየጠበበ በመምጣት ላይ እንደሆነ ብዙ ጥናቶችም ሆነ ተጨባጩ ሁኔታ ያረጋግጣል። ስለሆነም ፍራንሲስ ፉኩያማ እንዳለው በሊበራል ዲሞክራሲ አማካይነት የታሪክ መጨረሻው ላይ የተደረሰበት ዘመን ሳይሆን ብዙ አገዛዞች ወደ አምባገነንነት እየተለወጡ ወይም ደግሞ አምባገነን ፓርቲዎች ስልጣንን በመጨበጥ ታሪክን ለራሳቸው በሚስማማ መልክ የሚጽፉበት ዘመን በግልጽ በመታየት ላይ ነው። አንዳንድ ፈላስፋዎች እንደሚሉት ከዚህ አደገኛ ሁኔታ ለመውጣት የዓለም ማህበረሰብ እንደገና አዲስ የመንፈስ ተሃድሶ(Renaissance) እንቅስቃሴ ያስፈልገዋል።
ወደ አገራችን ስንመጣ የአገዛዞች መለዋውጥ፣ ወይም አበበ ተወግዶ በከበደ መተካት ህዝባችንን ነፃነት አያጎናጽፈውም፤ የዕድገትና የብልጽግና ዕድልም እንዲጎናፀፍ አያደርገውም። አንዳንዶች እንደሚሉትም በህገ-መንግስት መለወጥ ወይም መሻሻል ህዝባችን ዕውነተኛ ነፃነቱን አይቀዳጅም፤ የስልጣኔም ባለቤት ሊሆን አይችልም። ለነፃነትና ለህዝባችን ሰላም መቀዳጀት የሚደረገው ትግል ከዚህ አልፎ መሄድ ያለበት ጉዳይ ነው። ትግሉ ሁለንታዊ ወይም ሁለ-ገብ(Holistic) መሆን አለበት። ትግሉ በፍልስፍና፣ በተፈጥሮ ሳይንስ፣ በአርት፣ በአርክቴክቸርና በሙዚቃ እንዲሁም ልዩ ልዩ በሆኑ የሰውን ልጅ አዕምሮ በሚያድሱና ልቡን ርህራሄ በሚያደርጉ የቀን ተቀን ስራዎች መታጀብ አለበት። በተለይም ከግሪክ ስልጣኔና ይህንን እንደመመሪያ አድርገው የሳይንስና የቴክኖሎጂ፣ እንዲሁም የተሟላ ዕድገት ባለቤት የሆኑትን የአንዳንድ አውሮፓ አገሮችን የህበረተሰብ አወቃቀር ታሪክ ስንመረምር መንፈስ ካልታደሰ ጤናማ የሆነ የህብረተሰብ ዕድገት ላይ መድረስ እንደማይቻል ነው። በጭንቅላት ተሃድሶ አማካይነት ብቻ ነው ማንኛውም ሰው ከውስን አስተሳሰብ ሊላቀቅና ራሱን በመመርመር ተፈጥሮን በመቃኘት ዕውነተኛ ለውጥም ማምጣት የሚችለው። የአንድ አገር ታሪክ ተከታታይነት ያለውና ለተከታታዩ ትውልድም የሚተላለፍ እንደመሆኑ መጠን ተከታታዩ ትውልድ በደንብ የተበጀና የተስተካከለ አገር እንዲረከብ ማድረግ ከተፈለገ የግዴታ የመንፈስ አብዮት ማካሄድ ያስፈልጋል። አንድ አገር በተራ አክቲቪስቶች ነፃነትን የተቀዳጀበትና ብልጽግናን የተጎናፀፈበት ዘመን የለም። የአንድ አገር ህዝብ ዕድል መወሰን ያለበትና ህዝቡም ትክክለኛውን ፈለግ እንዲከተል ማድረግ የተወሳሰበ ዕውቀትን ለመቀዳጀት በሚችሉና ግን ደግሞ ነገሮችን ግልጽ አድርገው ማቅረብ
በሚችሉና በቀላል ቋንቋ ለሰፊው ህዝብና ለታዳጊው ትውልድ ለማስረዳት በሚችሉ ግለሰቦችና የተደራጁ ሰዎች አማካይነት ብቻ ነው።
የዚህ ድረ-ገጽ ባለቤት በዚህ ዐይነት ድረ-ገጽ አማካይነት ብቻ የአገራችንን የወሳሰበና አስቸጋሪ ጉዳይ ይቀርፋል የሚል ዕምነት ባይኖረውም ብዙ ግለሰቦችና ለአገርና ለወገን የሚያስቡ የሚሳተፉበት ከሆነ የታሪክን ግዴታ መወጣት ይቻላል። በህብረተሰብ ግንባታ ውስጥ እንደታየው ፈላስፋዎችም ሆነ የተፈጥሮ ሳይንስ ተመራማሪዎች ለራሳቸው ዝናና ክብር ብለው በፍጹም አልታገሉም፤ መታወቅ አለብንም ብለውም ምርምራቸውን አልጀመሩም። የምርምራቸው ውጤትም ተጠቃሚ ለመሆን አልቻሉም። ተጠቃሚ መሆን የቻለው ከሶስትና ከአራት መቶ ዐመታት በኋላ ብቅ ያለው ትውልድ ነው። ስለሆነም እኛም ትግል ስንጀምር ወይም ቀደም ብለን የጀመርንም ካለን ከእኛ ፍላጎት አንፃርና ዝናን ከመቀዳጅት ምኞት አኳያ መነሳት የለብንም። ለመጭው ትውልድ ምን ነገር አስተላልፈን መሄድ እንችላለ፟ን ? ብለን ነው እራሳችንን መጠየቅና መነሳት ያለብን። የዚህ ድረ-ገጽ ባለቤት ከ25 ዐመታት በላይ እንዳደረገው አቅሙና ጤንነቱ እስከፈቀደለት ድረስ የበኩሉን አስተዋፅዖ ከማድረገ አይቆጠብም። በዚህም መንፈስም ይሰራል።
ለአገራችንና ለህዝባችን ሰላምና ነፃነት እየተመኘሁ ይህ ድህረ-ገጽ ለምሁራዊ ውይይትና ጽሁፍ ክፍት መሆኑን አስታውቃለሁ። በዚህ ድረ-ገጽ ላይ ሊወጡ የሚችሉ ጽሁፎች በፍልስፍናና በሳይንስ ላይ የተመሰረቱ ብቻ ናቸው። አቀራረባቸው መንፈስን የሚያድሱና ልብን ርህሩህ የሚያደርጉ መሆን አለባቸው። ከዚህም በላይ ትችታዊ አስተሳሰብ(Critical Thought) ያላቸውና ጥያቄ እንድንጠይቅና መልስም እንድናገኝ የሚያደርጉ ጽሁፎች መሆን አለባቸው። አንድ አገዛዝ ወይም መንግስት ተግባራዊ የሚያደርገውን አገር አፍራሽና ህዝብን በታኝ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ፖሊሲ ዝምብለን የምናይበት ወይም አሜን ብለን የምንቀበልበት ሳይሆን በሳይንሱ መመርመር የሚያስችለንና አማራጭ ፖሊሲ ለመስጠት የሚያስችለን አቀራረብ መሆን አለበት። በመሆኑም በድረ-ገጹ ላይ የፍልስፍና፣ የፖለቲካ፣ የሳይንስና የህብረተሰብ፣ እንዲሁም የኢኮኖሚክስ ጉዳዮችን የሚመለከቱ ጽሁፎች ይታተማሉ። የኢኮኖሚክስ ጽሁፍን በሚመለከት በድረ-ገጹ ላይ የኒዎ-ሊበራል አቀራረብ በፍጹም አይታተምም። በዚህ መንፈስ ተባብረን ከሰራን አዲስና ጠንካራ፣ እንዲሁም ሰላምና ብልጽግና የሰፈነባትን ኢትዮጵያን የመገንባት ኃይልና ለተከታዩ ትውልድ የማስተላለፍ አቅም ይኖረናል የሚል ዕምነት አለኝ።
አዘጋጂው !
ማሳሳቢያ፣ ይህ ሃሳብ በድረ-ገጽ ላይ ብቻ ተወስኖ መቅረት ያለበት ጉዳይ አይደለም። ሃሳቡ ፍሬያማ የሚሆነው በተቋም ደረጃ በትምህርት መልክ ለታዳጊው ትውልድ የተሰጠ እንደሆን ብቻ ነው። ስለሆነም የድረ-ገጹ ባለቤት ሃሳቡን ዕውን ለማድረግ የግዴታ አገር ቤት አንድ ትልቅ የጥናትና የምርምር ተቋም መመስረት እንዳለበት ያምናል። ለጥናት የሚያስፈልጉ ልዩ ልዩ መጽሀፎች መገዛት አለባቸው። ከፍልስፍና እስከ ፖለቲካና፣ የኢኮኖሚና የሳይንስ መጽሀፎች ለመማሪያ በጣም አስፈላጊ ናቸው። በተጨማሪም ዘመናዊ የማስተማሪያ መሳሪያዎች ያስፈልጋሉ። በአጭሩ አንድ ተቋም ለመመስረት የግዴታ ተከታታይነት ያለው ወጪ ያስፈልጋል። ልዩ ልዩ ክፍሎችና የስብሰባ አዳራሾች ያለው ተለቅ ያለ ቤት መከራየት ያስፈልጋል። ቋሚ ሰራተኛና ዘበኛም መቀጠር አለባቸው። ለዚህ ሁሉ ባጀት ያስፈልጋል። ተቋሙ ከተመሰረተና ጥቂት ከተጓዘ በኋላ በራሱ ሊንቀሳቀስ የሚችልበት መንገድ ይፈለጋል። በወር አንድ ጊዜ የሚታተም ጋዜጣና በየሶስት ወሩ የሚወጣ መጽሄት የገቢ ምንጮች ሊሆኑ ይችላሉ። ሌሎችም መንገዶች እንደዚሁ ይፈለጋሉ። ይሁንና ሁልጊዜ የሚያስቸግረው በመመስረቻው ወቅት ወጪዉን መሸፈኑ ላይ ነው። በተለይም የቤት ኪራይ መክፈልና የቢሮ መሳሪያዎችን ከጠረቤዛዎችና እስከመቀመጫዎች ድረስ የመግዛቱ ጉዳይ ብዙ ገንዘብን ይጠይቃል። ስለሆነም እንደዚህ ዐይነቱን ዓላማ ተግባራዊ ለማድረግ ከአዘጋጂው አቅም በላይ ነው። ይህ አዘጋጅ ባለፉት 25 ዓመታት ከፍተኛ ወጪንና መስዋዕትነት የጠየቀ ምርምር አድርጓል። በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ጽሁፎችን አውጥቷል። በብዙ ሺህ የሚቆጠር ገንዘብ አፍሷል። የተለያዩ ጽሁፎቼን ለተመለከተ ጊዜን የፈጁና ብዙ ወጪዎችም የፈሰሰባቸው ናቸው።
በዚህ መንፈስ ወደፊት ለመቀጠልና ለተከታታዩም ትውልድ አንድ ቅርፅ ጥሎ ለማለፍ የግዴታ የሌሎችን የማቴሪያል፣ የመንፈስና የዕውቀት ዕርዳታን ይጠይቃል። የሚሰበሰበው ገንዘብ ለዚህ ዓላማ ብቻ የሚውል ስለሆነ ይህንንም በተግባር ማስመስከር ይቻላል። ለትብብሩ ከመጀመሪያውኑ አመሰግናለሁ።
ዕርዳታ መለገስ የምትፈልጉ በዚህ የባንክ ቁጥር ማስተላለፍ ትችላላችሁ!
IBAN: DE 13 1005 0000 0320 3255 39
BIC: BELADEBEXXX
Berliner Sparkasse
Fekadu Bekele-Negussie